Isaiah 12

የውዳሴ መዝሙር

1በዚያን ቀን እንዲህ ትላለህ፤

እግዚአብሔር ሆይ፤
ቀድሞ ተቈጥተኸኝ ነበር፤
አሁን ግን ከቍጣህ ተመለስህ፤
ደግሞም አጽናንተኸኛልና አወድስሃለሁ።
2እነሆ፣ እግዚአብሔር ድነቴ ነው፤
እታመናለሁ፣ ደግሞም አልፈራም፤
እግዚአብሔር በሚለው ስም ፈንታ ተተክቶ የገባ ነው።
ጌታ እግዚአብሔር ብርታቴና ዝማሬዬ ነው፤
ድነቴም ሆኗል።”
3ከድነቴ ምንጮች
ውሃ በደስታ ትቀዳላችሁ።
4በዚያን ቀን እንዲህ ትላላችሁ፤

እግዚአብሔርን አመስግኑ፤ ስሙንም ጥሩ፤
ያደረገውንም በአሕዛብ መካከል አስታውቁ፤
ስሙ ከፍ ከፍ ማለቱንም ዐውጁ።
5 ለእግዚአብሔር ዘምሩ፤ ታላቅ ሥራ ሠርቷልና፤
ይህም ለዓለም ሁሉ ይታወቅ።
6የጽዮን ሕዝብ ሆይ፤ እልል በሉ፤
በደስታም ዘምሩ፤
በመካከላችሁ ያለው የእስራኤል ቅዱስ ታላቅ ነውና።”
Copyright information for AmhNASV